ጃን ሜዳን የማጽዳት ስራ በ ም/ከንቲባ አዳነች አቤቤ መሪነት ተጀመረ

Sariyose

ጃን ሜዳን ለጥምቀት በዓል ዝግጁ ለማድረግ የማጽዳት ስራ በ ም/ከንቲባ አዳነች አቤቤ መሪነት ተጀመረ



የአዲስ አበባ ከተማ ም/ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከጽዳት ባለሙያዎችና ከጃንሜዳ አካባቢ ማህበረሰብ ጋር በመሆን ጃን ሜዳን የማፅዳት ስራ አከናውነዋል።


በጃን ሜዳ ውስጥ ያሉ አትክልት ነጋዴዎች ከጥቂት ቀናት በኋላ ወደ ተዘጋጀላቸው የአትክልት መሸጫ ስፍራዎች እንደሚዘዋወሩም ወ/ሮ አዳነች ተናግረዋል።


ጃንሜዳ ለጥምቀት በዓል ዝግጁ ለማድረግ እና ወደ ቀድሞ አገልግሎቱ ለመመለስ በተከታታይ የማጽዳት ስራ በልዩ ትኩረት እንደሚሰራም ምክትል ከንቲባዋ ገልጸዋል።


በጃንሜዳ ያሉ ነጋዴዎች በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ በሃይሌ ጋርመንት እና በሌሎች አካባቢዎች ወደተዘጋጁ የገበያ ማዕከላት ይዘዋወራሉ ያሉት ወ/ሮ አዳነች፣ በገርጂ፣ ጀሞ፣ አቃቂ፣ ጉለሌ እና ሌሎች አካባቢዎች ተጨማሪ አዳዲስ የአትክልት መገበያያ ስፍራዎች እየተዘጋጁ መሆኑንም በትዊተር ገጻቸው ገልጸዋል፡፡