ሰበር ፎቶ

Sariyose


ሰበር ፎቶ
እያደር ይፋጃል ፣ የጉድ ሀገር ገንፎ
የጉድ ሀገር ሽፍታ
ለህዝቡ ይሾማል ፣ የህዝብ ቤት ዘርፎ😂
የጉድ ሀገር ዜና ፣ እያደረ ሰበር
የጉድ ሀገር ግፊያ ፣ እያደረ ለወንበር
።።።
የጉድ ሀገር ዳታ ፣ እያደር ይጠፋል
የጉድ ሀገር አፅናኝ
ለበጎ ነው ብሎ ፣ ክፋት ሰርቶ ያልፋል
የጉድ ሀገር ስብከት ፣ "ፍቅር ያሸንፋል"
የጉድ ሀገር ተረት
"ሰይጣን ለአመሉ ፣ ቅዱስ ቃል ይጠቅሳል
የጉድ ሀገር ታሪክ
"ገዳይ ሲያረፋፍድ ፣ ሟች ይገሰግሳል።"
የጉድ ሀገር ሌባ
ዳቦ ስለሌለ ፣ ዳቦ ቤት ይልሳል😂
።።።።።።።
እያደር ይበላል ፣ የጉድ ሀገር ቴሌ
የጉድ ሀገር ተስፋ ፣ ይነጋል ነው ሁሌ
ጉድ አንድ ሰሞን ነው ፣ የጉድ ሀገር ተረት
ለአንዲት ቀን እንኳን ፣ ጉድ ባይችልም መቅረት
እያደር እንቧ ነው ፣ የጉድ ሀገር በረት
።።።።።።
የጉድ ሀገር ወሬ ፣ እያደር ሰቀቀን
የጉድ ሀገር ንጋት ፣ እያደር አንድ ቀን
እያደር እያደር
አድሮ ቃሪያ መሆን ፣ መይም ከርሞ ጥጃ
የጉድ ሀገር ምላሽ ፣ እያደር እኔንጃ
የጉድ ሀገር ፍርሀት ፣ እያደር ጠብመንጃ
የጉድ ሀገር ለቅሶ ፣ እያደር ወይ ፍርጃ።
።።
የጉድ ሀገር ዘፈን ፣ ሀገሬን ሀገሬን
የጉድ ሀገር ለቅሶ ፣ ብሔሬን ብሔሬን
የጉድ ሀገር ችግር ፣
ላይነጋ አይመሽም ፣ ብሎ ማንቀላፋት
የጉድ ሀገር መፍትሔ፣
ሻማ ለመፈለግ ፣ ፀሀይ ሰርቆ መጥፋት😂