በላይ በቀለ ግጥም

Sariyose



ደሃን ሳይበድል
ከበቡኝ ብሎ ሰው ሳያስገድል
ለልዩ ጥቅም ሳያውደለድል
ዱላ ሳይጨብጥ መንገድ ሳይዘጋ
እልፉን ነፃ አውጪ አእላፉን መንጋ
ያንቀጠቀጠው ፣ እስክንድር ነጋ
ወህኒ ሲጥሉት
ብዕር ጨብጦ ፣ ቃል እየሳለ
ቅኔ እንደ ሩዝ እየቀቀለ
በታች ነህ ሲሉት ፣ በላይ በቀለ