የናይል ተፋሰስ ሃገራት የሚኒስትሮች ምክር ቤት ዛሬ ይሰበሰባል | Nile Basin Initiative



     የናይል ተፋሰስ ሃገራት ኢኒሽዬቲቭ (NBI) የሚኒስትሮች ምክር ቤት (NBI-COM) ዛሬ 28ኛ መደበኛ ዓመታዊ ጉባዔውን በኦን ላይን የግንኙነት ዘዴ (ቨርቹዋል) ያካሂዳል፡፡
ጉባዔው ኢትዮጵያን ጨምሮ የተፋሰሱ አባል በሆኑ 10 ሃገራት የውሃ ሚኒስትሮች የሚካሄድ ሲሆን በበጀት እና ተያያዥ ስትራቴጂክ ጉዳዮች ላይ ይመክራል፡፡
የኢትዮጵያ የውሃ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ስለሺ በቀለም በስብሰባው እንደሚሳተፉ አስታውቀዋል፡፡
በኢንሽዬቲቩ የሚከናወኑ ተግባራት “ለናይል ውሃ ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ወሳኝ ናቸው” ያሉት ሚኒስትሩ “ኢትዮጵያ ለውይይት እና ለጋራ ርዕዮች ስኬት ቁርጠኛ መሆኗን” በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ ገልጸዋል፡፡
በጉባዔው ርዋንዳ የምክር ቤቱን የበላይ መሪነቷን ከኬንያ በይፋ ተረክባ ለቀጣዩ አንድ ዓመት የምትመራ ይሆናል፡፡
ኢትዮጵያን ጨምሮ ቡሩንዲ፣ ዴ.ሪ ኮንጎ፣ ግብጽ፣ ኬንያ፣ ርዋንዳ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ሱዳን፣ ታንዛኒያ እና ኡጋንዳ የኢንሽዬቲቩ አባል መሆናቸው የሚታወስ ነው፡፡
ኤርትራ ደግሞ በታዛቢነት ትሳተፋለች፡፡