ወጋገን ባንክ የጦር_መሣሪያ ተከማችቶ ተገኝ



 ወጋገን ባንክ የጦር_መሣሪያ ተከማችቶ ተገኝ

የፋይናንስ አገልግሎት ሰጭ በሆነው ወጋገን ባንክ ዋና መሥሪያ ቤት፣ ለጥበቃ አገልግሎት ከሚያስፈልገው ውጭ በዛ ያለ የጦር መሣሪያ ተከማችቶ መገኘቱ ተሰማ።

በአዲስ አበባ በርካታ የጦር መሳሪያ የተገኘባቸው ሌሎች ድርጅቶችም አሉ ተብሏል።

በወጋገን ባንክ  ዋና መሥሪያ ቤት የተገኙት የጦር መሣሪያዎች ለሌላ ዓላማ ሊውሉ የሚችሉ መሆናቸውን ኮሚሽነሩ ተናግረዋል።

በወጋገን ባንክ ዋና መሥሪያ ቤት ለጥበቃ አገልግሎት ከሚያስፈልገው ውጭ የጦር መሠሪያ ተከማችቶ መገኘቱን የነገሩን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጌቱ አርጋው፣ ከተገኙት መሣሪያዎች አንዳንዱ በፀጥታ ኃይሉ እጅ የሌሉ ጭምር ናቸው ብለዋል፡፡

ሱር ኮንስትራክሽንም የተለያየ ተልዕኮ ወስዶ ሲንቀሳቀስ የነበረ ሌላው የሕወሓት አካል ነው ተብሏል።

በከተማው ውስጥ ካሉ ባለሀብቶች መካከል ለሕወሓት ድጋፍ የሚያደርጉ እንደነበሩም ኮሚሽነሩ ተናግረዋል፡፡

ባለሀብቶች በተለያየ መንገድ ንብረት ሊያፈሩ ይችላሉ ያሉት ኮሚሽነር ጌቱ፣ የፖሊስ ኮሚሽኑ ከወንጀል ጋር የተያያዘ ተጨባጭ መረጃ እና ሕገ መንግሥታዊ ስርአቱን አደጋ ላይ የሚጥል ጥፋት በመፈፀም ተቀናጅተው የሚሠሩ አካላት ላይ ያተኮረ ሥራ ነው የሚያከናውነው ብለዋል፡፡