ህፃናት ወድቆ ያገኙት ቦምብ ፈንድቶ ጉዳት እንዳደረሰባቸው የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ

 

 

ህፃናት ወድቆ ያገኙት ቦምብ ፈንድቶ ጉዳት እንዳደረሰባቸው የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ

 በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ልዩ ቦታው በተለምዶ 02 ወይም ካፒቴን ደምሴ ሰፈር ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ህፃናት ወድቆ ያገኙት ቦንብ እጃቸው ላይ ፈንድቶ ጉዳት እንዳደረሰባቸው የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።


ህፃናቱ በሚጫወቱበት ሜዳላይ ተጥሎ ያገኙት የእጅ ቦምብ በአንድ የ13 ዓመት ህፃን ላይ ከፍተኛ እንዲሁም በአራቱ ላይ ቀላል የኣካል ጉዳት ማድረሱን የክፍለ ከተማው ፖሊስ መምሪያ የወንጀልና ትራፊክ አደጋ ምርመራ ኃላፊ ኮማንደር ባሳዝነው አክሎክ ገልፀዋል።


አምስቱ ህፃናት ወድቆ ያገኙትን ቦምብ መጫወቻ መስሏቸው ሲጓተቱ ቦምቡ መፈንዳቱን ኃላፊው ገልጸዋል፡፡


አራቱ ህፃናት ህክምና ተደርጎላቸው ወደ የቤታቸው የሄዱ ሲሆን ከፍተኛ ጉዳት የደረሰበት ህፃን በዳግማዊ ምንሊክ ሆስፒታል ህክምናውን እየተከታተለ ይገኛል፡፡