በኤርትራ የአሜሪካ ኤምባሲ በሀገሪቱ የሚገኙ ዜጎቹ በቤት ውስጥ እንዲቆዩ አሳሰበ።
የአሜሪካ ዜጎቹ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ የግድ አስፈላጊ ካልሆነ ጉዞ እንዳያደርጉ መክሯል።
ኤምባሲው ማሳሰቢያውን የሰጠው በአስመራ ለሚገኙ ዜጎቹ ዛሬ ሰኞ ህዳር 14 ባሰራጨው የማስጠንቀቂያ መልዕክት ነው።
ለዚህ ማሳሰቢያው መነሻ ምክንያት የሆነው በኤርትራ መንግስት ባለስልጣናት ትዕዛዝ ለአስመራ ነዋሪዎች የተነገረ መልዕክት ነው።
የUS በአስመራ ኤምባሲ ያገኛቸውን ሪፖርቶች ጠቅሶ እንዳስታወቀው በተወሰኑ የአስመራ ክፍል የሚገኙ የአካባቢ ጥበቃዎች፤ የከተማይቱ ነዋሪዎች ምሽቱን በቤታቸው እንዲያሳልፉ ነግረዋቸዋል።
የአስመራ ነዋሪዎች ከቤታቸው ውጭ እንዳያንቀሳቀሱ የተነገራቸው በምን ምክንያት እንደሆነ ኤምባሲው የሰጠው ማብራሪያ የለም።
የኤርትራዋ መዲና ባለፈው ህዳር 5 ምሽት ከትግራይ ክልል በተወነጨፉ ሚሳኤሎች መመታቷ ይታወሳል። የሚሳኤል ጥቃቱን "ህወሓት" መፈፀሙን እንደገለፀ ይታወሳል።