ትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በወቅታዊ ጉዳይላይ የተሰጠ መግለጫ
**********************************************************************************
የትግራይ ክልልና ህዝብ በሚስሌነ ለማስተዳደር ማሰብ የቀን ቅዥት ነው
የትግራይ ህዝብና መንግስት በየትኛውም የታሪክ ስህተትና አጋጣሚ፣ ለፋሽሽታዊ ተግባርና ወራሪ እጅ ያስገባበት መጥፎ ታሪክና ጠባሳ ያለው ህዝብ አይደለም፡፡ ይልቁንስ ለህዝቦች ሰላምና እኩልነት፣ ለነፃነትና ፍትህ፣ እንድሁም ለደሞክራስያዊ አንድነት ውድ ልጆቹን መስዋእት በመክፈል የነፃነትና የአርበኝነት ሰንደቅ ሆኖ ለሃገርም ለራስም የሚተርፍ የአኩሪ ታሪክና ድል ተምሳሌት ስለመሆኑ የአደባባይ ሚሲጢር ነው፡፡
የትግራይ ህዝብ ህገ መንግስታዊ መብቱ ተጠቅሞ ምርጫ በማካሄድ በወከላቸው መሪዎቹ መንግስት መስርቶ፤ የክልሉ ህዝብ ህልውናና ድህንነት አደጋ ላይ ለጣለው ፋሽሽት አሸባሪና ወራሪ የአብይ አህመድ ቡድንና የአምበገነኑ ኢሳያስ አፈወርቂ ቡድን የትግራይ ህዝብ በፅናትና በአንድነት የተከፈተበትን የዘር ማጥፋት ጦርነት ለመቀልበስ በፅናት እየታገለና ወራሪ ኃይሉ የሽንፈትና የውርደት ካባ እያከናነበ ባለበት ወቅት፤ ሕጋዊነቱ ባበቃና፤ ኢ-ሕገ መንግስታዊ በሆነ በፈረሰዉ የቀድሞ የፌዴሬሽን ም/ቤት በትግራይ ክልል ጊዚያዊ መንግስት እንዲሰየምና ፋሽሽት አሸባሪውና ወራሪ የአብይ አሕመድ ቡድን የትግራይ ህዝብ ለማስተዳደር ይቻል ዘንድ የህልምና የቅዥት ውሳኔ አስተላልፈዋል፡፡
ይህንን ተከትሎ በህዝቦች ትግል ተንኮታኩቶ የወደቀው የንጉሡ ሥርዓትና የደርግ አገዛዝ ተግባር፣ በህልመኛው ንጉሥ አብይ አሕመድ ሂወት ለመዝራት በመሞኮር ከአዲስ አበባ ምስሌኔ መሪዎች በመሾም ህጋዊው የትግራይ መንግስትና አመራር ለመቀየር ሲንደፋደፉና ሽሙናል ሲሉ ይሰማሉ፡፡
ይህ የፋሽሽት አሸባሪና ወራሪ አብይ አህመድ ትግራይን በወንጭፍ ለመምራት መከጀል ከንቱ ቅዥት ነዉ፡፡ የትግራይ ህዝብና መንግስት በመስዋእትነቱ ያረጋገጠው መብትና ድል ማንም ቢሆን ፈቅዶ የሚሰጠውና የሚነሳው አይደለም፡፡ ሆኖም የተለያዩ አጀንዳዎች በመፍጠር የትግራይ ህዝብ ትግልና አንድነት ለመሸርሸር የሚደረግ እኩይ ተግባር ከመሆኑ ያለፈ ውጤት የለውም፡፡
በመጨረሻ የፍሽሽት አሸባሪውና ወራሪው የአብይ አሕመድ ቡዱንና የአምባገነኑ ኢሳያስ አፈወርቂ ወረራና ትንኮሳ ግብአተ መሬት የሚገቡበት ጊዜ ሩቅ አይደለም፡፡ የትግራይ ህዝብም ዛሬም ነገም ከራሱ ፍቃድና ይሁንታ ውጪ ከአሸባሪው ቡዱን ይቅርና በማንኛውም በዚች ምድር ላይ ያለ የሆነ ሃይል ያለ ምርጫው እና ፍላጎቱ ለማስተዳደርም ሆነ በካርዱ ለመረጣቸው መሪዎቹ ለመቀየርም ለመሾምም ማሰብ የቀን ቅዥት ነው፡፡
ትግራይ የአድሐርያን መቃብር እንጂ መፈንጫ አትሆንም!
(የትግራይ ኮሚኒዩኬሽን ጉዳዮች ቢሮ)