ግጭቱን ዓለም አቀፍ ለማድረግ የሚያደርገውን ጥረት አሜሪካ አወገዘች !


 ግጭቱን ዓለም አቀፍ ለማድረግ የሚያደርገውን ጥረት አሜሪካ አወገዘች !


ትላንት ሕወሓት በኤርትራ ላይ የፈጸመውን ተቀባይነት የሌላቸው ጥቃቶች እና በትግራይ ክልል የተፈጠረውን ግጭት ዓለም አቀፍ ለማድረግ የሚያደርገውን ጥረት አሜሪካ አጥብቃ እንደምታወግዝ በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚነስትር ቲቦር ናጊ ገለፁ፡፡

ረዳት ሚኒስትር  ናጊ "ሰላማዊ ሰዎችን ለመጠበቅ ፣ ውጥረቶችን ለማርገብ እና ሰላምን ለማስፈን አፋጣኝ እርምጃ እንዲወሰድ ማበረታታችንን እንቀጥላለን" ሲሉ በትዊተር ገፃቸው ላይ ፅፈዋል።