መቀሌ የሚገኙ የአሜሪካ ዜጎችን ወደ ሌሎች አካባቢዎች ለማዛወር እንደሚሰራ የአሜሪካ ኤምባሲ አስታወቀ


በትግራይ ክልል ወታደራዊ እንቅስቃሴዎች መቀጠላቸውን እና የኢንተርኔትም ሆነ የስልክ የግንኙነት መስመሮች መቋረጣቸውን ያስታወቀው የአሜሪካ ኤምባሲ በክልሉ የሚገኙ የአሜሪካ ዜጎች ደህንነቱ በተጠበቀበት ስፍራ ሆነው ራሳቸውን ሊጠብቁ እንደሚገባ አስታወቀ፡፡
ኤምባሲው መቀሌ የሚገኙትን የሃገሪቱን ዜጎች ወደ ሌሎች አካባቢዎች ለማዛወር በሚችልባቸው ዕቅዶች ዙሪያ እየሰራ እንደሚገኝም አስታውቋል፡፡
ስለሆነም በክልሉ ሆነው የሳታላይት ግንኙነት ያላቸው ዜጎች አለበለዚያም ወደ መቀሌ ያመራ ቤተሰብ ያላቸው ሰዎች እንዲያሳውቁትም ጠይቋል፡፡