የሰሜን ዕዝን የሬዲዮ መገናኛ በመጥለፍ የተጠረጠሩ 7 የጄኔራል መኮንኖች ፍርድ ቤት ቀረቡ
የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን የሰሜን ዕዝን የሬዲዮ መገናኛን በመጥለፍ እና የመገናኛ ሥርዓት እንዲቋረጥ በማድረግ ዕዙ በጁንታው የሕዋሓት የጥፋት ቡድን ጥቃት እንዲፈፀምበት ሲያመቻቹ ተገኝተዋል በሚል የጠረጠራቸውን 7 የጄኔራል መኮንኖች ዛሬ ፍርድ ቤት አቅርቧል።
የመከላከያ ኮሙዩኒኬሽን ኃላፊ ሜጀር ጄነራል ገብረመድህን ፍቃዱን ጨምሮ ሃገርን በመክዳት ወንጀልና ህገ መንግስታዊ ስርአቱን ለመናድ በማሰብ ወንጀል የተጠረጠሩ የመከላከያ ሰራዊት አመራሮች ፍርድ ቤት ቀረቡ፡፡
በዛሬው እለት ፍርድ ቤት የቀረቡት የመከላከያ ኮሙዩኒኬሽን ኃላፊ ሜጀር ጄነራል ገብረመድህን ፍቃዱ፣ የመከላከያ ሰራዊት ምዕራብ ዕዝ አዛዥ ሜጀር ጄኔራል ይርዳው ገብረመድህን፣ የደቡብ ዕዝ ሰው ኃብት ልማት አዛዥ ብርጋዴር ጀኔራል ገብረዮኃንስ ሳርሲኒዮስ፣ የሰሜን ዕዝ መረጃ ዘርፍ ኃላፊ ብርጋዴር ጀኔራል ኢንሱ ኢጳጆ ረሾን ጨምሮ ሰባት ሀገርን በመክዳት ወንጀልና ህገመንግስትና ህገመንግስታዊ ስርዓቱን በሀየይል ለመናድ ማሰብ ወንጀል በቁጥጥር ስር ውለው ፍርድ ቤት ቀርበዋል፡፡