ሐረማያ ዩኒቨርስቲ ለሀገር መከላከያ ሠራዊት 5 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ለማድረግ ወሰነ


 

 

ሐረማያ ዩኒቨርስቲ ለሀገር መከላከያ ሠራዊት 5 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ለማድረግ ወሰነ

***********************************************************************************
ሐረማያ ዩኒቨርስቲ ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ያለውን አጋርነት ለመግለጽ አምስት ሚሊዮን ብር ድጋፍ ለማድረግ መወሰኑን አስታወቀ።
የዩኒቨርስቲው መምህራንና ሠራተኞች በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ዙሪያ ዛሬ ውይይት አካሂደዋል።
በውይይት መድረኩ የዩኒቨርስቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ጀማል ዩሱፍ እንደገለጹት፣ የሀገር መከላከያ ሠራዊትን በየአቅጣጫው ድጋፍ ማድረግ የሚያስፈልግበት ወቅት ነው።
‹‹እኛም የምንችለውን ሁሉ ድጋፍ በማድረግ ለሠራዊቱ አጋርነታችንን በተግባር ማሳየት ይገባናል›› ብለዋል።
የዩኒቨርስቲው አስተዳደር የአምስት ሚሊዮን ብር ድጋፍ ለማድረግ መወሰኑንም አስታውቀዋል ዶ/ር ጀማል።
በውይይቱ የተሳተፉ የዩኒቨርስቲው መምህራንና ሠራተኞችም ለሀገር ክብርና የህግ የበላይነትን ለማስከበር እየተዋደቀ ለሚገኘው ለጀግናው የመከላከያ ሠራዊት ከደመወዛቸው ቆርጠው ድጋፍ ለማድረግ መወሰናቸውን ኢዜአ ዘግቧል።