አቢሲኒያ ባንክ አጠቃላይ ተቀማጭ ገንዘቡ ከ47 ቢሊዮን በላይ ብር መድረሱን አስታወቀ።
አቢሲኒያ ባንክ 24ኛው አመታዊ መደበኛ የባላክሲዮንች ጠቅላላ ጉባኤውን በአዲስ አበባ በማካሄድ ላይ ይገኛል።
ባንኩ በዚህ ጊዜ እንዳስታወቀው አጠቃላይ ተቀማጭ ገንዘቡ ባለፈው አመት ከነበረው 32.15 የነበር ሲሆን ዘንድሮ 47 ነጥብ 63 ቢሊየን ማደረሲን አስታወቋል።
የባንኩ የካፒታል መጠን ደግሞ ከብር 4 ነጥብ 95 ቢሊየን በ14.7 በመቶ በማሳደግ ወደ ብር 5 ነጥብ 68 ከፍ ማድረግ መቻሉም ተገልጿል።
ባንኩ ባለፈው ዓመት 14 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ አቅዶ 16 ቢሊየን ብር መሰብሰቡን ገልጿል።
የጭማሪው ዋና ምክንያቶች በበጀት አመቱ 1 ነጥብ 3 ሚሊየን አዳዲስ ደንበኞችን በመሳቡ መሆኑን ባንኩ በጉባኤው ላይ አስታውቋል።
በተጨማሪም ባንኩ ባለፉት 12 ወራት ከ1 ቢሊዮን በላይ ብር ያልተጣራ ትርፍ ማግኝቱን የገለጸ ሲሆን ትርፉ ከባለፈው አመት ጋር ሲነጻጸር የ6 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል ።