በደቡብ ክልላዊ መንግሥት የካምባታ ጠምባሮ ዞን እና የካፉ ዞን ለሀገር መከላከያ ሠራዊት 4.8 ሚሊዮን ብር የሚገመቱ የቁም እንስሳት ድጋፍ አደረጉ፡፡
የከምባታ ዞን ለመከላከያ ሠራዊት አለኝታነታቸውን ለመግለጽ 3.5 ሚሊዮን ብር የሚገመቱ 24 ሰንጋ በሬ ፣ 101 በግ እና 364 ፍየሎች ድጋፍ አድርገዋል ፡፡
የካፋ ዞን ህዝብ ከቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ለሃገር መከላከያ ሠራዊት አጋርነታቸውን ለመግለጽ 1.3 ሚሊዮን ብር የሚገመቱ 31 ሰንጋ በሬዎች አበርክተዋል፡፡
ድጋፉን የተረከቡት የሃገር መከላከያ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ማርታ ሊዊጂ ለሠራዊቱ ለተደረገው ድጋፍ አመስግነው ሶጦታው ቀጥታ ወደ ግምባር የሚሄድ መሆኑን ገልጸዋል፡፡