በደቡብ ክልል በጉራ ፋርዳ ወረዳ ከ300 በላይ አማራዎች ተመረዙ

 


 
 “በደቡብ ክልል በጉራ ፋርዳ ወረዳ ከ300 በላይ አማራዎች በአንድ ክፍል ውስጥ በምግብ ተመርዘው ራሳቸውን ስተው መገኘታቸውን ከቦታው በስልክ ያነጋገርናቸው የአሻራ ሚዲያ ምንጮች ገልፀዋል”
የሚል በዚሁ በማህበራዊ ሚዲያ ሲዘዋወር እየተመለከትኩ ነው። ከወር በፊት በዚያ አካባቢ የሚኖሩ የአማራ ተወላጆች ተፈናቅለው ጉራ ፋርዳ ወረዳ ቢፍቱ ከተማ ትምህርት ቤት ውስጥ አሁን ድረስ ተጠልለው ይገኛሉ።
እኔም ወደዚያው ደወልኩ ።
ምንም የተፈጠረ ነገር የለም ።
ደውየ ካጣራሁት ከቢፍቱ ከተማ ውጭ የተጠለሉ ሰዎች በጉራ ፈርዳ ወረዳ የሉም ።
ብዙዎቹ ወረዳውን ለቀው ወደ ሚዛን ከተማ የገቡ ናቸው።